በግእዝ ቋንቋ ላይ ለድፍን 2 ዓመታት ያደረግነው እረፍትየለሽ እንቅስቃሴ ፈጣሪ ይመስገን እዚህ ደርሷል።
የአማራ ት/ት ቢሮ

ለክ/ዘመናት የሚዘልቅ ወርቃማ ታሪክ ሰርታችኋል … እያደረ እየደመቀ የሚሄድ … ያውም የ250 ዓመታት ሴራን በአፍጢሙ የደፋ!!
ልዩነቱ ግን ይገርማል!! ብልህ ሰው ታሪክ የሚሰራበት እድል ካገኘ ለደቂቃ አያመነታም!! እንደ ህወሓት ያለ ጅል፣ ሆዳምና ባንዳ ሰው ደግሞ ለጊዜያዊ ጥቅሙ ብቻ እሴት የሚነቅልበት ቅንጣት እድል ካገኘ አይኑ ሳያሽ ሚሊዮናችን የሚያጭድ ቀይ-ሕገመንግስት ቀይ-ስህተት ቀይ-ስርዓት ይገነባል!!!
ዶ/ር ዋቅጅራ በግእዝ ዙሪያ ወደ ሰጧቸው አስተያየቶች ከማለፌ በፊት ስለ አንድ ገጠመኝና ውጤቱ ላስነብባችሁ።
አንድ ሁላችሁም የምታውቋቸው ታላቅ ምሁር የሚባልለት ሰው ( ፒኤችዲ) ነው። በህይወት ስሌለ ነው ስሙን የማላነሳው። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በዘመናዊ ፍዚክስ ዘርፍ ብቸኛ ምሁር ነበር። በ2006ዓ/ም ውስጥ በአንድ ተቋም በኩል ለስራ ተገናኘን። የረጂም ዓመታት ስራዎቼን አስረከብኩት። ሁለት ወራት ሙሉ ካነበበ በኋላ ያለኝን መቼም አልረሳውም፣ “ኃይማኖቴ አይፈቅድም፣ ማህበረሰብ በሚያበለሽ ስራ ላይ፣ ሃይማኖትን በሚበርዝ ስራ ላይ፣ እጄ አላስገባም” አለኝ በስልክ። “ጥሩ! ብንገናኝ ግን ብዙ ቁምነገሮች አገኝ ይሆናል” አልኩት በትህትና። “እሺ ግን ሰሞኑን የፒኤችዲ ተማሪዎች ጥናት evaluate እያደረኩኝ ነው እንደምታወቀው ጊዜው አሁን ነው” አለኝና ተስማማን። ቀጥሎ አንድ ጥያቄ አነሳሁ … “ግን ከሳይንሳዊ ሞዴሎች ውጭ የፃፍኩት ነገር አለ?” አልኳቸው። “የለም! በጥልቀት እንደተረዳኸው አይቻለሁ! የቅርብ ጊዜ ጥናታዊ ስራዎችም ጭምር ያካተተ በመሆኑ ለኛም የሚጠቅም ነገር አለው፤ ግን ህዝቡ በሚናገረው ቋንቋ በአማርኛ መፃፉ ባህልንና ኃይማኖትን ይበክላል” አለኝ። በጣም ደነገጥኩ። ምን ማለት ነው? ባጋጣሚ እጅግ ብዙ የተጠነቀቅኩበት ጉዳይ ነበር።
በእርግጥ እኝህ ሰው፣ በማህበረሰብ ዘንድ አዲስ እውቀት/ባህል ሲፈጠር ኃይማኖት በባህሪው ተከታትሎ ወደራሱ አዙሮ አዲስ ትርክት መፍጠር ላይ ፈፅሞ ተወዳደሪ እንደሌለው ላይገነዘቡ ይችላሉ። ግን የፕሮቴስታንት እምነት የሬዲዮን አምድ ይዘው ሲያራምዱ የነበሩት ሀሳብ የህዝቡ እምነት ይበረዛል ብለው ለምን አላሰቡም ነበር? ስለዚህ ጉዳዩ ሌላ ነው ወደ ማለት አዘነበልኩ።
ስለዚህ እኝህ ሰው ትምህርቱን በትትርና ሸምድደው ተማሩት እንጂ “internalize-philosophize” አላደረኩትም ነበር፤ ወደ አመለካከት አለወጥቱም ነበር፤ ማለት ምክንያታዊ ነው። ምናልባትም የተጋነነ ልመስል ይችላል እንጂ፣ ከልጅነታቸው ጀምሮ በውስጣቸው ከሰረፀው አመለካከት ጋር የተዋሄደ አንድ ትምህርታዊ አስተሳሰብ በውስጣቸው የለም ማለት ይቻላል። ይህ ደግሞ የብዙዎቻችን ችግር መሆኑን በድፍረት ሳይሆን በእውቀትና በልምድ የምመሰክረው ጉዳይ ነው።
ከዚህ የስልክ ልውውጥ በኋላ “የትምህርትና የምርምር ስርዓታችን ለምን በእንግሊዝኛ ሆነ? በእንግልዝኛ በመሆኑስ ያጣነው ነገር አለወይ?” የሚል ሀሳብ ላይ በተደጋጋሚ ማሰብና መመርመር ጀመርኩ። ሁሉም ያደጉ አገራት የቋንቋ ስርዓታቸውን ለመዳሰስ ሞከርኩ፤ የሚገርመው ግን የምርምርና የትምህርት ስርዓታቸው 100% በራሳቸው ቋንቋ ብቻ መሆኑን ተረዳሁ።
ቀጥሎ፤ ቋንቋና የአዕምሯችን ሀሳቦች ዝምድና እንዳላቸው የሚመረምሩ literatures ላይ ንባብ ጀመርኩ። በእርግጥ እዚህ ላይ ሁሉም ግልፅ ሆነልኝ።
(1) ዓለምን የምናይበት የአመለካከት ርብርቦሽ (layers of mental imges) decode የሚደረጉት በአፍመፍቻ ቋንቋችን ወይም በአገሩ ሚዲያዎች በሚዘወተር ቋንቋ ስለመሆኑ፤ (0.1% እንኳን ለማህበረሰባዊ ግንኝነት ማንጠቀምበት የእንግልዝኛ ቋንቋ የመርምርና የትምህርት ስርዓታችን ማእከል ላይ ማድረግ ምን ማለት ነው?)
(2) ከአፍመፍቻ ቋንቋችን ወይም በአገሩ ሚዲያዎች ከሚዘወተር ቋንቋ በራቀ ቋንቋ መማር ማለት ትምህርቱና መሰረታዊ ሀሳባችን ዘይትና ውሃ እንደማይቀላቀሉት ሁሉ ለየብቻ layer ይፈጥሩና በተማርነው መሰረት ችግሮችን ሞዴል አድርገን መፍትሔ ማምጣት የማንችል ስንኩላን ከማድረግ ውጪ፣ እሴቶቻችንን እንደችግር የምንቆጥርበት አመለካከት ከመያዝም በላይ ትምህርቱ ምንም ጥቅም የማይኖረው መሆኑን፤ የመቶ ዓመታት የዘመናዊ ሳይንስ ትምህርታችንም ፋይዳየለሽ መሆኑን፤
(3) አፄ ኃይለስላሴ እንግልኛን ወደ የትምህርትና የምርምር ማእከሉ ሲያስገቡት ኤርትራን ወደ እናት አገሯ ለመመለስ የተከፈ እጅግ ውድ መስዋእትነት መሆኑን፤ (Ethiopian history፣ Ethiopian literature የሚያስተምሩ ከእንግሊዝ ከፈረንሳይ ማስመጣት ተገደው ነበር)
(4) እኤአ በ1835 የካቲት 02 የእንግሊዝ ፓርላማ ላይ በቀረበው “በእንግልኛም ሆነ በራሱ ቋንቋ ለማሰብ አጉል የሆነ፣ የራሱን እሴት የሚጠላና የራሱን እሴት መለየት የማይችል ምሁራን በመፍጠር እንዴት አንዲት አገር 100% truely dominated nation መፍጠር እንደሚችሉ” የሚል ይዘት ያለው ሀሳብ በማንበቤም መንገዳችን አጠቃላይ የስህተት መንገድ መሆኑን፤
ተረዳሁ ማለት ነው።
አሁን ወደ ዶ/ር ዋቅጅራ ልመለስ።
ዋና ሀሳቡ አንድ ነው፡ “ተናጋሪ ማህበረሰብ የሌለውን ቋንቋ መማር ድካም ነው ጥፋት ነው” የሚል ነው።
……………………..
ደብተራ (በኋላ ፖስተር) ፍሰሃጊዎርግስ እና ደብተራ (በኋላ ፓስተር) ማቴዎስ ስለሚባሉ ባንዳዎች በተከታታይ መፃፌ ታስታውሱ ይሆናል። እነዚህ ሰዎች የፈጠሩትን ጠባሳ ምናልባት አሁን ዶ/ር ዋቅጅራ ያቀረበውን ሀሳብ ካየን በኋላ በቀላሉ መረዳት እንችላለን። ደብተራ ማቴዎስ በአንድ እንግሊዛዊ ኤጄንት ከአክሱም ተመልምሎ ስውዲን አገር (ዶ/ር ዋቅጅራ የተማረበት) ሄዶ ስለ ስነቋንቋ ለዓመታት ከተማረ በኋላ የግእዝ ቋንቋን ባለቤትአልባ ለማድረግ የግእዝ ሰዋስውን በማጣመም #ልሳነትግራይ የሚባል አዲስ ቋንቋ ፈጥሮ መፅሀፍ ቅዱስን በተበላሸ መልኩ ተረጎመ። በ1888 ዓ/ም (ከአድዋ ድል በኋላ) ውስጥ ደብተራ ፍሰሃጊዎርጊስ ደግሞ በጣሊያኖች ከአድዋ ተመልምሎ ኤርትራ ከተወሰደ በኋላ ወደ ጣሊያን አገር ተወስዶ የጣሊያንኛና የላቲን ቋንቋዎችን ለአመታት ከተማረ በኋላ “ጉዑዘዩ … ” የሚል የጉዞ ማስታወሻ “ልሳነትግራይ” ብሎ በጠራው አዲስ ቋንቋ ግእዝን ባለቤትአልባ ለማድረግ ጣሊያን ሆኖ ከመፃፉም በላይ በታሪክም ሆነ በትርክት ፈፅሞ የሌለውን ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ መንግስትን “የአማራ መንግስት” ብሎ በመፃፍ ለዚህ ጄኖሳይድ የዳረገን ሰው ነበር።
ለዛም ነው፣ ትግርኛ የሚባለው ቋንቋ ግእዝን በማጣመም (ግእዝን ባለቤት አልባ ለማድረግ) የተፈጠረ ቋንቋ ነው የምንለው። ለዚህም እልፍ ታሪካዊ ማሳያዎች አሉ። ፕሮፌሰር ፓንክረስ እንደፃፈው “ትግራይ ውስጥ የግእዝ ቋንቋ በ1890ዎች 38% ተናጋሪዎች የነበሩት ሲሆን በ1905 ላይ ወደ 6% ወረደ” ብሏል። ሰዋስው የዞረ ግእዝ በመናገር ዘመነኛ ለመሆን የሚደረግ ፍክክር ነበር። ቀጥሎ “የግእዝ ቋንቋ በቤተክርስቲያን ተወስኖ በመቅረቱ የሞተ ቋንቋ ነው” የሚሉ ጥናታዊ ስራዎች ታተሙ ተሰራጩም።
ስለዚህ ዶ/ር ዋቅጅራ ትክክል ነው። የተማረውን ነው የፃፈው ምሁር ተብሎ አለማሰብ ግን ያሳፍራል። እንዴት የተባለውን ይደግማል?? ቢያንስ የግእዝ ቋንቋ የበርካታ ቋንቋዎች እናት ቋንቋ መሆኑን መገንዘብ እንዴት ያቅተዋል?
ዶ/ር ዋቅጅራ ተቀበል! እርስዎ እንዳሉት ግእዝ ቋንቋ የሞተ ቢሆን እንኳን እንደ አደባባይ ምሁርነትዎ የሞተን ማስነሳት ነበረብዎት ። ከምሁር የሚጠበቀው ትንሣኤን ማብሰር እንጂ ሞትን ማወጅ አልነበረም ። ያልሞተን ሞተ ብሎ ማወጅ “የሰበር ዜና” ጋዜጠኞች እንጀራ ብቻ ይመስለኝ ነበር። ለማንኛውም ከፍትህ ጋዜጣ እና መጽሔት ጀምሮ ጽሁፍዎትን ሳነብ የነበርኩ ሰው ነኝ ፣ ዛሬ በዚህ መልኩ ሲገለጹ አዘንኩ ።
ለማንኛውም ግእዝ ቋንቋ አልሞተም ! ቢሞት ኖሮ ሊቃውንቱ ይራቀቁበት ነበር ወይ ? ቢሞት ኖሮ እርስዎ የሚያውቋቸውም የሚያደንቋቸውም የውጭ አገር ዩኒቨርሲቲዎች ጊዜ እና በጀት መድበውለት ይማሩት ነበር ወይ !? ቢሞት ኖሮ እርስዎን ጨምሮ ሌሎች ሰዎች በትምህርት ቤት እንዳይሰጥ ትቃወሙት ነበር ወይ !?
Anyway ከ7 ዓመታት በፊት ዶ/ር ዋቅጅራ፡ ጣሊያን በፍሰሃጊዎርጊስ በኩል፣ እንግሊዝ በደብተራ ማቴዎስ በኩል፣ ግብፅ በህወሓት በኩል፣ ጀርመን በወለጋ ጀርመናውያን ሰፋሪዎች በኩል በሀሰት ትምህርት እሴቶቻችንን በመበረዙ ምክንያት የመጣ ዲዛይን የተደረገ ማሕበራሲ ልሽቀት መሆኑን እንደምሁር ባለማየቱ፤ በ2011ዓ/ም ውስጥ በጥናት ስም “የኢትዮጵያ ህዝብ ወድቋል፤ በጥልቁ የሞራል ልሽቀት ውስጥም ገብቷል” እያለ ታላቁን የኢትዮጵያን ህዝብ ሲዋርድ ነው 100% እንከን የበዛበት “ምሁር” መሆኑን ያረጋገጥኩት፤ ኃይማኖትን እና ኃይማኖታዊ እሴቶችን እንኳን መለየት የማይችሉ ምሁር። Here We go ❤ root causዙ ከተረዳን የሚያቆመን ኃይል የለም።
ህወሓት በአስተሳሰብም እየሞተ የመሆኑ ማረጋገጫ፣
(1) “የግእዝ ቁጥር ከግሪክ የመጣ ነው” የሚል የባንዳ ተግባር የመማሪያ መፃህፍት ቢያስገቡም በርብርብ ነቅለን ስናወጣው፣
(2ኛ) የግእዝ እሴቶችን ለማጥፋት ይሄን ያክል መንገድ ለ40ዓመታት ስርዓት ገንብተው ከተጓዙ በኋላ “ፈፅሞ የማይቻል” የተባለውን የግእዝ ቋንቋ በመደበኛ የት/ት ስርዓት መካተቱ …!
(3ኛ) የአቢሲኒያ እሴቶችን ፈፀሞ ለማፍረስ የኢትዮጵያ ማእከላዊ እሴቶችን ለማፍረስ የተገነባው የህወሓት ሕገመንግስት ለትግራይ ህዝብ የጄኖሳይድ ብቸኛ ምንጭ መሆኑን ማሰብ የሚችል ሰው መረዳቱ
(4ኛ) አሁን ላይ ቀይቢጫ ተራ ጨርቅ ብቻ ሳይሆን የትግራይ ጄኖሳይድ ምልክት ተደርጎ መወሰዱ
(5ኛ) ጨምሩበት
ለሓበሻ ማሕበረሰብ የህልውናው አደጋ የሚመጣው ከግብፅ ሳይሆን ከህወሓት ነው ከህወሓት በላይ ግን ከእስራኤል ነው 100%!! የግእዝ ቋንቋ በመደበኛ ትምህርት መጀመሩ እንኳን እስራኤላውያን ዘንድ እንዴት ያለ ጫጫታ እንደተጀመረ እያየነው ነው!! ንጉሳዊ ቤተሰቦችንን ከስርመሰረታቸው የነቃቀለቻቸው ኃይለስላሴን ጨምሮ እስራኤል መሆኗን፣ ከኢትዮጵያ የሄዱት ቤተእስራኤላውያውያን ሴቶችን እንዳይወልዱ የሚከትቡ መሆኑን መቼም ቢሆን ባንረሳው መልካም ነው። በአንድም ይሁን በሌላ ከሐበሻ እሴቶች ጋር ጥቂትም ቢሆን ቁርኝት ካለህ እስላም ሁን ክሪስትያን ኦሮሞ ሁን አማራ ትግራይ ሁን አገው አፋር ሁን ጉራጌ … እጣፈንታህ አንድ ነው!! እነ
#ደብረሲኦል ብቻ ናቸው ጊዜያዊ ጥቅም የሚያገኙት!!
ሆን ብለው ትርጉም የሚያዛቡ አካላትን ተጠንቀቋቸው!!
ሴኩላሪዝም መንግስትነት ከኃይማኖት የሚለይበት እንጂ ከሃይማኖታዊ እሴቶች የሚለይበት አይደለም። ይህ ዓይነቱ ሴኩላሪዝም ሌላ ነው፣ አዲስ ነው፣ ለጄኖሳይድ የሚሰራ ትርጉም ነው። ዓለም ከሚያውቀው ሴኩላሪዝም የተቃረነ ትርጉም ነው።
ኃይማኖታዊ እሴቶችን የማይጠብቅ መንግስትነት ታዲያ ለዛ ማህበረሰብ ጠላት እንጂ የምን መንግስት ነው? ምክንያቱም በነዚያ ኃይማኖታዊ እሴቶች ውስጥ ለሺህ ዓመታት የተገነባ ማህበረሰብ አለ። መንግስትነት የነዚህ ማህበረሰብ እሴት ሊጠብቅና ሊያከብር የግድ ነው። ይሄንን ማህበራዊ ግንባታ ለማፍረስ የቆመ እንደሆነ ያ መንግስት ለዛ ማህበረሰብ literally ጄኖሳይደር ማለት ነው።
የግእዝ ቋንቋ እሴት ብቻ አይደለም የእሴቶች ሁሉ መቋጠሪያው ገመድም ጭምር እንጂ!!
ያሬዳዊ ዝማሬዎች ለአማኙ ኃይማኖታዊ ክንዋኔዎች ናቸው ለአጠቃላይ ለሀገሩ ግን እሴቶች ናቸው።
መንዙማዎች ለአማኙ ኃይማኖታዊ ክንዋኔዎች ሊሆኑ ይችላሉ ለአጠቃላይ አገሩ ግን እሴቶች ናቸው።
ስለዚህ ኃይማኖታዊ እሴቶችንና ኃይማኖትን እያጨናበሩ ያገሩ መሰረቶች የሚንዱ ተግባራትን በሴኩላሪዝም ስም ማበረታታ/መታገስ
#ኢመንግስታዊ ተግባር ነው።
የግእዝ ቋንቋ በት/ት ስርዓቱ ውስጥ መካተት ጥያቄ አስነሳ እየተባለ ነው።
ነሀሴ26/2017ዓ/ም
በአውሮፓና አሜሪካ ውስጥ ብቻ 31 ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች ግእዝን የሚያጠኑበት ምስጢር ምንድን ነው? አንድ ዩኒቨርስቲ ብቻ አይበቃም ነበር? ካቶሊክ በዩኒቨርስቷ ግእዝን ማጥናት ለምን ፈለገች? አሜሪካ ውስጥ የፕሮቴስታንት ቤተመፃህፍት ትልቁ ሃብታቸው የግእዝ መፃህፍት ስለምን ሆነ?
ይሄውላችሁ፡ ግእዝ ፈፅሞ የማይሞት ቋንቋ ነው። በስነቋንቋ ጠበብቶች a language that defies time የተባለለት ነው። quantum encryption ላይ ከአለም ቋንቋዎች ሁሉ ወደር በሌለው መልኩ effective ሆኖ የተገኘ ብቸኛ ቋንቋ ነው። የግእዝ ፊደል በአንድ ፊደል ብቻ 7ድምፆችን የቋጠረ የscientific model አርአያ ነው የsystemic representation አርያ ነው። ምን ማለት ነው፡ “ሀ” ውስጥ ሰባቱም ራሳቸውን የቻሉ ድምፀቶች አሉ። A ውስጥ ግን አንድ እንኳን ራሱን የቻለ ድምፅ የለም። A(ኤ) በአ ውስጥ ከተቋጠሩ 7ድምፆች ውስጥ አንዱ ድምፅ ነው። በእርግጥ ግእዝ ከላቲን አንፃር 700% ጥቅልል (compacted) ነው 7እጥፍ ጥቅልል ነው። ስትፈልግ ጥቅልሉን ትዘረጋዋለህ። ምክንያቱም ሲስተሚካሊ ሞዴል የተደረገ በመሆኑ። ግእዝ ከአንድ ግስ ብቻ 3600 ቃላት የሚመዘዙበት ልዩ ኃይል ያለው condensed ቋንቋ ነው። ዓለም ለበርካታ የመጪው ዘመናት ወሳኝ ጉዳዮቿ ግእዝን ትፈልገዋለች። እስካሁን በአማካይ 900,000 መፃህፍት ወላጆቻችን በግእዝ ቋንቋ ስለኢትዮጵያ፣ ስለመንፈሳዊ ጉዳዮችና ስለተፈጥሯዊ ጥባባት እንደፃፉ ጥናቶች ያሳያሉ፤ ከነዚህ ውስጥ 20%ቱ እንደጠፉም ይታመናል።
በመሆኑም ለኛ ሁሉም እሴቶቻችን በግእዝ ነው የተፃፉት፤ እንደ ህዝብም ሆነ እንደ አገር መሰረታችን ግእዝ ነው።
#አጋእዝያን የምንባለውም ለዚያ ነው። ታዲያ ግእዝን በት/ት ስርአታችን መግባቱ የት ላይ ነው ጉዳቱ? ስለምድን ነው ግእዝን መማር የማያስፈልገን? መልስ ሊኖራቸው አይችልም።
ሲጀመር “የግእዝ ት/ት ጥያቄ ተነሳበት” የሚባለው ውሸት ነው ራሳቸው ከውጭ ሆነው የፈጠሩት እንጂ አንድም ጥያቄ የጠየቀ አካል የለም። ግእዝ ቋንቋ ነው ለፈለከው ጉዳይ የምትጠቀምበት ቋንቋ። ከኃይማኖት ጋር ብቻ የተሰፋ አድርጎ መውሰድ የነማን ፍላጎት እንደሆነ ይታወቃል። ግእዝ እንኳን በኢትዮጵያ ይቅርና ገና የፓን አፍሪካኒዝም ምልክት ይሆናል። የሰውልጅ የልእልልና ምልክትም ነው። ይህን ሳልጠራጠር እነግራችኋለሁ።
(ለ) ፕሮቴስታንት የግእዝ እሴቶች ጠላት
የአማራ ክልል የት/ት ቢሮና የአማራ ክልል ምሁራን ምትክ የለሽ ታሪካዊ ስራ ሰርታችኋል። ብዙ ፈተናዎች እንደሚነሱ ግን ከወዲሁ ማወቅ አለባችሁ። ፈተናዎች የሚነሱት አንደኛው፣ ሁለተኛውና ሦስተኛው ከፕሮቴስታንት ወገን ነው። ፕሮቲስታንት የአቢሲኒያ እሴቶችን ለማጥፋት ኢትዮጵያ ውስጥ የተሰማራ ኃይል ነው። ፕሮቴስታንት የፈጠራቸው ብሄርተኛ አስተሳሰቦች አሉ፤ እነዚህ አስተሳሰቦች የፖለቲካ ድርጅቶች ተመስርቶባቸዋል፤ እነዚህ የፓለቲካ ድርጅቶች ሻዕቢያ፣ ኦነግና ህወሓት ናቸው። ማሳያ፡
(1ኛ) ገሚሶቹ እንግልዝ ኤርትራን በሚገዛበት ጊዜ በእንግሊዝ ኤጄንቶች ተመልምለው ስውዲን ድረስ ተወስደው ስነቋንቋና ብሄርተኝነት (linguistics & ethnicity) አጥንተው፤ ገሚሶቹ ደግሞ በጣሊያናውያን ተመልምለው ጣሊያን አገር ሄደው ስነቋንቋና ብሄርተኝነት (linguistics & ethnicity) አጥንተው፣ የግእዝ ሰዋስውን አጣምው “ልሳነ-ትግራይ” የሚል ስም ሰይመው፣ የኢትዮጵያ መንግስትን “የአማራ መንግስት” ብለው የሚፈርጁበት መፅሀፍ ፅፈው፣ ፀረእሴቱ የሆነ የትግራይ ብሄርተኛ አስተሳሰብን የፈጠሩት ፕሮቴስታንቶች ናቸው። እነ ደብተራ (ኋላ ፓስተር) ፍሰሃጊዎርጊስ እና ደብተራ (ኋላ ፓስተር) ማቴዎስ። ከህወሓት መፈጠር ጋር ተያይዞ በግልፅ እንደሚታየው ግእዝ ላይ የተመሰረቱ የአቢሲኒያ እሴቶችን ማጥፋት እንደግብ ይዞ የሚንቀሳቀስ፣ መሰረቱን ማፍረስ ላይ የተጠመደ የትግራይ ብሄርተኝነት ተፈጥሯል። ሆኖም በሂደት ወደእሴቱ መመለሱ የግድ ስለሆነ መመለሱ አይቅርም። እስከዚያው ግን ማጥፋቱን ይቀጥላል፤ ከዚህ በፊት በርካታ እሴቶች አጥፍቶ chaos ውስጥ እንደከተተን ሁሉ አሁንም የህወሓት አስተሳሰብ እስኪጠፋ ድረስ ማጥፋቱን ይቀጥላል።
(2ኛ) ከጀርመን ተፈናቅለው ወለጋ ላይ ሰፍረው መፅሀፍ ቅዱስን ተርጉመው የኢትዮጵያ መንግስትን በብሄር ፈርጀው የኦሮሞ ብሄርተኝነትን የፈጠሩት ፕሮቲስታንቶች ናቸው። ጥያቄው ብሄርተኝነቱ መፈጠሩ ሳይሆን፣ 72 ዓመታት የሰሎሞናዊ ስርወመንግስትን በራሳቸው ነፃፍላጎት ያስቀጠሉት እነ ራስአሊን የማያካትት የኦሮሞ ብሄርተኝነት ለምን ተፈጠረ ነው? ለግእዝ-ወለድ ስነፅሁፎች መዳበር በግንባርቀደምትነት አስተዋጽኦ ያደረጉት የኦሮሞ ኤሊቶች ሆነው እያለ ከግእዝ ፊደላት ይልቅ እጅግ ደካማ ዝርክርክና የቀኝገዢዎች የሆነውን የላቲን ፊደልን የመረጠ ብሄርተኝነት ለምን ተፈጠረ ነው ጥያቄው?
➤ኦሮሚኛ ቋንቋ በግእዝ ፊደላት 1ገፅ የሚፃፈውን መልእክት፣ በላቲን ፊደላት ሲፃፍ ግን በአማካይ 4ገፆችን ይወስዳል። ይህ ማለት ቴክኒካሊ የኦሮሞ ህዝብን በንቃትና በኢኮኖሚ 4እጥፍ ጫና ውስጥ መክተት ማለት ነው። ኦሮሚኛ ውስጥ በግእዝ ፊደላት የማይወከሉ ድምፆች አሉ የሚባለው ውሸት ነው። ግእዝ መሰረቱ የሴሜቲክና የኩሸቲክ ድብልቅ ስለሆነ ለኦሮሚኛ ቋንቋ ከግእዝ የሚቀርበው ዓለም ላይ የለም። የአማርኛው ፊደል “ሸ” ከግእዙ ፊደል “ሰ” እንደተፈጠረው ዓይነት በአንዱ ፊደል ላይ አንድ ጭረት በመጨመር የኢሮሚኛ ፊደል በመፍጠር ብቻ የሚፈታ ነው። የላቲን ፊደላትን ወደ የኦሮሚኛ ድምፀቶች ለማምጣት ምን ያህል ድርዕቶ እንደተጠቀሙ ለገባው ሰው እጅግ ያፍራል ይደነግጠልም። ይህ ድርዕቶ በአደጊ አዕምሯዊ ንቃት ላይ የሚፈጥረው ጠባሳ ደግሞ በሂደት ምን አይነት ማህበረሰብ ይፈጠራል የሚለው ጥያቄም እጅግ ወሳኝ ጥያቄ እየሆነ መጥቷል። በአዲስ አበባና በአዲስ አበባ ዙሪያ ያሉትን ት/ቶች በማነፃፀር በላቲን የሚማሩት ላይ ከ37-40% ኢንተለጀንስ እንደቀነሰ የጠቆመ አንድ AI-generated ጥናትም አንብቢያለሁ።
በአጠቃላይ ለኦሮሞ ህዝብ ፍፁም ጉዳትና አንዲት ጥቅም የሌላቸው ውሳኔዎችና ትርክቶች በብሄርተኝነቱ ውስጥ መሰረት ይዘዋል። ስለዚህ መሰረታዊ ጥያቄው፤ ከህዝቡ ጥቅምና ፍላጎት ጋር አብረው የማይሄዱ ፈፅሞ ለpower struggle ጥቅም ላይ ሊውሉ የማይገባቸው ስርነቀል ውሳኔዎች መወሰናቸው ለምን የሚል ነው? መልሱ ከስርመሰረቱ የፕሮቴስታንት ሚሽን ውስጥ እናገኘዋለን። “ኢትዮጵያ የሚለው ስያሜ ይቀየርልን” የሚለው ሽታም ከፕሮቴስታንታዊ ወገን የተፈሳ ነው።
(ሐ) ጠላታችን ፕሮቴስታንት ብቻ ነው??
በእርግጥ እንደአስተሳሰብ ፕሮቴስታንት ብቻ ነው ጠላታችን።
#ልብበሉ እኔ የሳይንስ እንጂ የኃይማኖት ሰው አይደለሁም። ስለ ኃይማኖታዊ እሴት እንጂ ስለ ኃይማኖት አያገባኝም። እስላም እንደ ኃይመሰኖታዊ እሴት ወይም እንደ አስተሳሰብ የኛ ነው፤ በአለም ደረጃም የኢትዮጵያ እስላም የራሱ ቀለም ያለው ነው፤ ያ ቀለም የኛ ቀለም ነው የራሳችን እሴት ነው። ከእስላም ጎን ተሾጉጦ ሊያጠፋን ቀንና ሌሊት እየሰራ ያለው ግን ፕሮቴስታንታዊ አስተሳሰብ ራሱ ነው፤ በብሄር ውስጥ ሆኖ ሊያጠፋን ቀንና ሌሊት የሚሰራውም እሱ ራሱ ነው። በእውነት ሌላ ጠላት የለነም። ስለዚህ ከኢትዮጵያ የእስልምናዊ አስተሳሰብ ጋር ህብረት መፍጠር ግዴታችን ነው፤ ወይም ህብረት የሚፈጠርበት አስተሳሰብ ማራመድ ግዴታችን ነው፤ እንደ እምነት ሳይሆን እንደ እሴት። ምክንያቱም የግእዝ እሴቶች መሰረታቸው ከኦርቶዶክስ በፊትም ስለሆነ ለሁላችንም ይመለከተናል። ፕሮቴስታንት ግን አፈጣጠሩ ሌላ ነው፡ የባሪያ ንግድን ለኢንዱስሪ አብዮት መፈጠርና መስፋፋት እንደ ወሳኝ ግባኣት ጥቅም ላይ የዋለ ነው፤ ለቀኝ ተገዢነት ስብከት ጥቅም ላይ የዋለ ነው። ጥንታዊ እሴቶችን በማጥፋት ዓለምን ወደ አንድ አዲስ ስርዓት (new world order) ለማምጣት የተዋቀረ ኃይማኖት መሳይ የሊበራል አይዲዮሎጂ ነው። ለዛም ነው ባለፊት 230 ዓመታት ውስጥ በሰው ልጆች ላይ የተደረጉ ጄኖሳይዶች ሁሉ እንደ root cause ሆኖ ፕሮቲስታንት ብቅ የሚለው። ለዛም ነው ሃዋሪያዊ የመፅሀፍ ቅዱስ መተርጎሚያ መነፀር ስሌለው እንደአሜባ እየተከፋፈለ በጥቂት ዓመታት 45ሺህ የተመዘገቡ ፕሮቴስታንታዊ እምነቶች የተፈበረኩት፤ ለወደፊቱ ሞቲቬሽናል ፍላጎቶች ላይ ስር እየሰደደ ከመፅሃፍ ቅዱስ እየተነቀለ ገና ብዛታቸው ወደ ሚሊዮኖች ይደርሳሉ … እዚህ ፕሮቴስታንታዊ ምእራፍ New World Order actualize የሚያደርገበት ነው።
በእርግጥ የነቁ ፕሮቴስታንቶችም የአቢሲኒያ እሴቶች ጉዳይ የመጨረሻው የህልውና ጉዳይ መሆናቸውን አውቀው ከኛው ወገን ላይሰለፉ አይችሉም።
ስለዚህ በአማራ ምሁራኖች በኩል እየመጣ ያለ ብርሃን ይታያል ከወዲሁ የፈተናዎቻችን ምንጭ መለየቱ ግን ብልህነት ነው ለማለት ነው።
Engineer Tafere Hiluf (የሓበሻ ብሔ ኣግዓዚ ሕብረት ፓርቲ -ANU Global Supreme Leadership)



