Manifesto

የአርማችን ትርጓሜ

ባለአራት ቀለማት ሰንደቅ ዓላማችን፣ የቀይ ባህር መርከባችን፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የንግስናና የስንዴ ምልክትን የያዘሲሆን ትርጉሙም እንደሚከተለው ይብራራል፦

  • ቀይ፦ በደማችን የግእዛዊት ኢትዮጵያ ሀገራችንንና ዘላቂ ጥቅሟን እናስከብራለን።
  • ነጭ፦ ልብሳችንና የደስታችን መገለጫ (ለሠርግ፣ ለእንግዳ አቀባበል እና ለሌሎች በዓላት) የምንጠቀምበት።
  • ሰማያዊ፦ የግእዛዊት ኢትዮጵያችን ቀይ ባህር።
  • አረንጓዴ፦ ልማት / ለምለሟ ግእዛዊት ኢትዮጵያ።
  • መርከብ፦ ከዓለም ጋር የምናካሂደውን የንግድ ግንኙነት እና የተፈጥሮ ግዛታችንን ሉዓላዊነት የምናስከብርበትየግእዛዊት ኢትዮጵያ ምልክት።
  • ሁለቱ ነገሥታት (የግእዛዊት ኢትዮጵያ) የነገሥታቶቻችን ምስል ሲሆን በራሳቸው ላይ አክሊልና የጀግንነትምልክት ይታያል። ክቡ መጠምጠሚያው በተለይ ክርስትናን ከመቀበላችን በፊት በነበረው የአልሙቃህ ባህላዊእምነት ዘመን ይዘወተር የነበረ የግእዛዊት ኢትዮጵያ የጀግንነት ምልክት ነው። ‘ዘውዱ’ ደግሞ ክርስትናንከተቀበልን በኋላ ነገሥታቶቻችን የንግሥና ቅብዓት ሲቀቡ የሚጠቀሙበት የግእዛዊት ኢትዮጵያ ሥነ-ሥርዓትነው።
  • ስንዴ፦ ዘመናዊ ግብርና በዓለም ላይ በብሔረ አግዓዚ (ግእዛዊት ኢትዮጵያ) እንደተጀመረ እና ወደፊትም ዘመናዊቴክኖሎጂን ተጠቅመን የተሻለ ምርት ለማምረት ያለንን ራዕይ የሚያመለክት ታላቅ ትርጉም የያዘ የብሔረ አግዓዚውድብ (Agaezi National Union) አርማ ነው።

የብሔረ አግዓዚ (Agaezi National Union Flag) እና የአፄ ዮሐንስ ሰንደቅ ዓላማ

የንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ ሰንደቅ ዓላማ ከቀይ ባህራቸው ጋር፦ የብሔረ አግዓዚ ውድብ (Agaezi National Union Party) በቀደሙት መድረኮቹ ባሳለፋቸው ውሳኔዎች መሠረት፣ ህዝባችንን ከገባበት ሁለንተናዊ ቀውስና የጥፋት አደጋአውጥቶ ወደ ነበረበት መደበኛና የላቀ ሥልጣኔና እሴቶቹ ለመመለስ የተሸከመውን ታላቅ የትውልድ ኃላፊነትለመወጣት፣ ከሰንደቅ ዓላማችን ጀምሮ በይፋ ሥራ ጀምሯል።

ይህ ሰንደቅ ዓላማ የአባታችን የንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ አራተኛ የነበረ ሲሆን፣ የንጹሕ ህዝባችንን ደም ናፋቂና ጠጪየሆነውን የህወሓት-ማሌሊትን ቀይ ባንዲራ በመተካት ወደ ዘላቂ ሰላም፣ ብልጽግና፣ እድገትና ህልውናእንደሚያሸጋግረን ምንም ጥርጥር የለውም። ህወሓት-ማሌሊት በንጉሠ ነገሥቶቻችንና በእነሱ የተሰሩትን እሴቶቻችንንሁሉ የሚጠላ መሆኑ የሚታወቅ ሀቅ ነው።

ስለሆነም “ከ1967 ዓ.ም. በፊት የነበረው ሥልጣኔ፣ እሴት፣ ታሪክ፣ ቅርስ፣ ትርክት፣ ሰንደቅ ዓላማ፣ የግዛት ክልል፣ማዕከላዊነት፣ የሕግ የበላይነት፣ ቀይ ባህር ወዘተ ይመለከተኛል፤ እያንዳንዱ ጦርነት አያስፈልገኝም” የሚለው የግእዛዊትኢትዮጵያ ህዝብ፣ ይህችን ቀይ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ ቀለማትና የአንበሳ ምልክት ያላትን ሰንደቅ ዓላማ የራሱ እንደሆነችእንገልጻለን። ይህችን የማናውቃት፣ ከግእዛዊት ኢትዮጵያ ምድርና ህዝብ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላትን፣ የደም አፍሳሽኮሚኒስት፣ ማርክሲስት ሌኒኒስት ጨርቅ የሆነችውን የህወሓት-ማሌሊት ባንዲራ ብሎ የተሰዋ የግእዛዊት ኢትዮጵያህዝብ እንደሌለ በድፍረት ልንሞግትና ልናረጋግጥ ይገባል። ኢትዮጵያም ሆነች ኤርትራ የግእዝ እንጂ የላቲን፣ የዓረብወይም የኮሚኒዝም ግዛቶች ወይም እሴቶች እንዳልሆኑ በትክክል ተረድተን መታገል የግድ ይለናል።

በትግራይ (ህወሓት) እና በብሔረ አግዓዚ (የብአው) ሰንደቅ ዓላማዎች መካከል ያለው ልዩነት

  1. የህወሓት-ማሌሊት (የትግራይ) ባንዲራ ከተስፋ (ቢጫ) ወደ ሙሉ በሙሉ ጨለማና ጥፋት (ቀይ) የሚያመላክትሲሆን፣ የብሔረ አግዓዚ (የብአው) የግእዛዊት ኢትዮጵያ ባንዲራ ግን “በደማችን ተስፋችንንና ልማታችንንእናረጋግጣለን” የሚል ትርጉም አለው። አንበሳውም አሸናፊነታችንን (Mighty warriors) ያረጋግጣል። ይህየህወሓት (የትግራይ) ባንዲራ ከትንሽ ቀይ ወደ ትልቅና ሰፊ ቀይ የሚወስደን፣ ተስፋም ሆነ ልማት የሌለው፣ በደምእንድንታጠብ የሚያደርገን አደገኛ ምልክት ነው። የብሔረ አግዓዚ (የብአው) ባንዲራ ግን ልማትንና ተስፋንየሚከተልና የሚቀርጽ ነው።
  2. ይህ የህወሓት-ማሌሊት (የትግራይ) ባንዲራ ከ1977 ዓ.ም. ጀምሮ የነበረ ሲሆን፣ ከኮሚኒስት ቻይና፣ ቬትናም እናአልባኒያ የተቀዳና ከሐበሻ ብሔረ አግዓዚ (የግእዛዊት ኢትዮጵያ ምድር) ባህልና የእሴት ሥርዓት ጋር ምንም ዓይነትግንኙነት እንደሌለው ይታወቃል።
  3. ይህ የብሔረ አግዓዚ ውድብ (የብአው) ሰንደቅ ዓላማ ደግሞ የመጀመሪያው የዓለማችን ሰንደቅ ዓላማ ሲሆን፣በተለይም በአክሱም ጽዮን ለአባታችን ለንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ የተሰጠ እንደሆነ ይታወሳል። ይህም ከሐበሻብሔረ አግዓዚ / ግእዛዊት ኢትዮጵያ ሥነ-ልቦናና ታሪክ ጋር እጅግ የተዋሐደና የተቆራኘ መሆኑን መረዳት የግድነው።
  4. የህወሓት (የትግራይ) ባንዲራ እጅግ ጠባብ ካርታ (minority)፣ መግቢያና መውጫ የሌለው (landlocked) እንዲሁምዳርቻ (periphery) መሆንን ሲያመለክት፣ የብሔረ አግዓዚ ውድብ (የብአው) ባንዲራ ግን እጅግ ሰፊ ግዛት(Majority)፣ የቀይ ባህር ባለቤት፣ የኢኮኖሚና የዲፕሎማሲ ማዕከል (Core State) የሚያደርገን የግእዛዊት ኢትዮጵያአስፈላጊ ምልክታችን መሆኑን ተረድተን መታገል አለብን እንላለን።

ዓላማው ግልጽ ነው!

  1. የግእዛዊት ኢትዮጵያ ፊደል
  2. የግእዛዊት ኢትዮጵያ የመንግሥት ሥርዓት
  3. የግእዛዊት ኢትዮጵያ ታሪክና ትርክት
  4. የግእዛዊት ኢትዮጵያ ባህር
  5. የፓርቲ ሣይሆን የሓበሻ= ብሔረ ኣግዓዚ=ግእዛዊት ኢትዮዽያ ህዝብ ኣገራዊ ህግ (Public National Constitution)

ይህንን እውን፣ ተግባራዊ እና አስተማማኝ ማድረግ ነው። ማንኛውም ሰው ሌላ ዝርዝር ሳያስፈልገው እነዚህን 4 የብሔረ አግዓዚ ውድብ መሠረታዊ ዓላማዎች ይዞ መታገል ይችላል። የብሔረ አግዓዚ ውድብ (Agaezi National Union Party) ዝርዝር ማኒፌስቶን ለማንበብ ጊዜና ትዕግስት ካገኘ ደግሞ እሰየው!!

የግእዝ ህዝብና ምድር (ብሔረ አግዓዚ) ግእዛዊት ኢትዮጵያ ትንሣኤ በብሔረ አግዓዚ ውዳበ(በውብ) ይረጋገጣል!!

The Meaning of Our Emblem

Our four-colored flag, our Red Sea ship, the obelisks of Axum, containing the symbol of royalty and wheat, is interpreted as follows:

  • Red: With our blood, we will secure our nation of Ge’ezawit Ethiopia and its lasting interests.
  • White: Our attire and the expression of our joy, used for (weddings, guest receptions, and other celebrations).
  • Blue: The Red Sea of our Ge’ezawit Ethiopia.
  • Green: Development / The lush (verdant) Ge’ezawit Ethiopia.
  • Ship: A symbol of Ge’ezawit Ethiopia for the trade relations we conduct with the world and the means to secure the sovereignty of our natural territory.
  • The Two Kings (of Ge’ezawit Ethiopia): It is the image of our kings, and on their heads are a crown and a symbol of heroism. The round headwrap, in particular, was a symbol of heroism of Ge’ezawit Ethiopia used in the era of our traditional Almouqah faith before we accepted Christianity. The ‘crown’, however, is the ceremony of Ge’ezawit Ethiopia that our kings use after being anointed with the oil of kingship after our acceptance of Christianity.
  • Wheat: An emblem of the Agazi National Union (Agaezi National Union) that holds great meaning, signifying that modern agriculture was started in the world by the Agazi Nation (Ge’ezawit Ethiopia) and representing our vision to produce better yields in the future using modern technology.

Emperor Yohannes IV-Summons to Defend the Motherland

  • “Hark, O people of Ethiopia! Consider this with all your heart, observe, listen, and comprehend.Your nation, Ethiopia, is your mother first.
    She is your honor second.
    She is your wife third.
    She is your child fourth.
    And she is your final resting place fifth. Knowing she embodies a mother’s love, a crown’s dignity, a wife’s devotion, a child’s delight, and the sanctity of the grave, you must arise!

Defend your motherland! Vanquish the invader!”

The Flag of the Agazi Nation (Agaezi National Union Flag) and the Flag of Emperor Yohannes

The flag of the King of Kings, Emperor Yohannes, with his Red Sea: Based on the decisions passed by the Agazi National Union Party in its previous forums, in order to fulfill its great generational responsibility of liberating our people from the all-encompassing crisis and destruction they have entered and returning them to their normal and superior civilization and values, it has officially begun its work, starting with our flag.

This flag belonged to our father, the King of Kings, Emperor Yohannes IV. There is no doubt that by replacing the red flag of the TPLF-MALELIT—which yearns for and drinks the blood of our pure people—it will transition us to lasting peace, prosperity, development, and existence. It is a known fact that TPLF-MALELIT is against our emperors and all the values created by them.

Therefore, the people of Ge’ezawit Ethiopia who say, “The civilization, values, history, heritage, narrative, flag, territorial domain, centrality, rule of law, the Red Sea, etc., that existed before 1974 (1967 E.C.) concern me; I do not need every war,” we want to declare that this flag, which contains the colors red, yellow, green and the symbol of the lion, is their own. We must courageously argue and prove that there is no person from Ge’ezawit Ethiopia who was martyred for this TPLF-MALELIT cloth—a blood-shedding, communist, Marxist-Leninist [flag] that we do not know and that has no connection whatsoever with the land and people of Ge’ezawit Ethiopia. It is imperative that we understand correctly that both Ethiopia and Eritrea are dominions and values of Ge’ez, not of Latin, Arab, or Communism, and we must struggle accordingly.

 

 

The Difference Between the Flag of Tigray (TPLF) and the Agaezi Nation (ANU) of Ge’ezawit Ethiopia

  1. The flag of the TPLF-MALELIT (Tigray) indicates a move from hope (yellow) to complete darkness and destruction (red), whereas the flag of the Agazi Nation (ANU) of Ge’ezawit Ethiopia signifies, “With our blood, we secure our hope and our development.” The lion confirms our status as victors (Mighty Warriors). This flag of the TPLF (Tigray) is an extremely dangerous symbol that takes us from a little red to a large and wide red, that has neither hope nor development, and that makes us wash ourselves in blood. The flag of the Agazi Nation (ANU), however, follows and shapes development and hope.
  2. This flag of the TPLF-MALELIT (Tigray) dates from 1985 (1977 E.C.) and it is known that it was copied from communist China, Vietnam, and Albania, and that it has no connection whatsoever with the culture and system of values of the Habesha Agazi Nation (the land of Ge’ezawit Ethiopia).
  3. This flag of the ANU (Agazi Nation), however, is the world’s first flag, and it is remembered that it was specifically given in Axum Zion to our father, the King of Kings of Ethiopia, Emperor Yohannes of the Agazi Nation. It is imperative to understand that this is deeply integrated and intertwined with the psychology and history of the Habesha Agazi Nation / Ge’ezawit Ethiopia.
  4. This flag of the TPLF (Tigray) represents an extremely narrow map (minority), landlocked (no entry or exit), and also a periphery, while the flag of the ANU (Agazi Nation) represents an extremely vast territory (Majority), owner of the Red Sea, and a center of economy and diplomacy (Core State). We say we must struggle with the understanding that this is our very important symbol of Ge’ezawit Ethiopia.

The Main Objectives of ANU are Clear!

  1. The Script of Ge’ezawit Ethiopia
  2. The System of Administration of Ge’ezawit Ethiopia
  3. The History and Narrative of Ge’ezawit Ethiopia
  4. The Sea of Ge’ezawit Ethiopia
  5. The Public National Constitution of Ge’ezawit Ethiopia

It is to make these real, practical, and secure. Any person can struggle holding these 4 fundamental objectives of the ANU without needing any other details. And if they find the patience to read the detailed manifesto of the Agazi National Union Party, all the better!!

The Resurrection of the People and Land of Ge’ez (Agaezi Nation) of Ge’ezawit Ethiopia will be guaranteed by ANU!!

 

Scroll to Top